አጠቃላይ የፕሮጀክት ግንባታው አራት ደረጃዎች (4 Basement) ያሉት የመኪና ማቆሚያን ጨምሮ ሱቆች፣ ካፍቴሪያ፣ አምፊ ቲያትር፣ የኢንተርኔት አገልግሎት መስጫ፣ የስራ ቢሮዎችና ሌሎች ሁለገብ አገልግሎቶችን መስጠት እንዲያስችል ምቹና ውብ ተደርጎ የታነፀ ሁለገብ አገልግሎት መስጫ ህንፃ ነው ፡፡
ከከፍተኛ አመራሩ ጀምሮ በየደረጃው ባሉ የግንባታው ዘርፍ አካላት ልዩ ድጋፍና ክትትል እየተደረገለት የማጠቃለያ ምዕራፍ ላይ የሚገኘው የታላቁ ቤተ መንግስት ቅርስና መኪና ማቆሚያ ፕሮጀክት አሁን ላይ ለተቋሙና ለውጭ ተገልጋዮች የሚሆኑ ማረፊያ ወንበሮች፣ ጠረጴዛ፣ ቁሳቁስ ማስቀመጫ ቁም ሳጥኖች ፣ መመገቢያ ጠረጴዛዎች እና መሰል መገልገያ ቁሳቁሶችን የማስገባትና ተቋሙን የማደራጀት ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛል!!
ቁሳቁሶችን ከማስገባት ጎን ለጎን በህንፃ ውስጥ የተዘረጉ የመካኒካል መሰረተ ልማቶችና ሌሎች የህንፃው አስተዳደር መረጃ (BMI)ስርዓትን መቆጣጠርና በአግባቡ ማስተዳደር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ለተለያዩ ባለሙያዎች ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል፡፡