በመንግስትና በግሉ ዘርፍ አጋርነት የጀመርነውን ስራ በማስፋት ዓለም አቀፍ ልምድና ብቃት ካለው የቻይናው ግዙፍ ኩባኒያ(FHEC) ጋር በሽርክና ለመስራት 35 ሔክታር መሬት በወቅታዊው የሊዝ ዋጋ አስልተን ያቀረብን ሲሆን፣ አልሚው ፋይናንስ ፣ ቴክኖሎጂ እና ልምድን ይዞ ግንባታውን የሚያከናውን ይሆናል።
ዓለም አቀፍ ተደራሽነት ያለው ይህ “አዲስ ቱሞሮ” የተባለ ፕሮጀክት ዘመኑ የደረሰበትን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ግንባታውን የሚያከናውን ሲሆን፣ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኑ በውስጡ አለም አቀፋዊ የኢኮኖሚና የንግድ ዞን ፣ የትምህርትና የባህል ዞን ፣ የፋይናንስና ቢዝነስ ዞን እንዲሁም ዘመናዊ የመኖሪያ ቤት ዞንን የሚያካትት ነው።ፕሮጀክቱ ለሀገራችን የኢኮኖሚ እምብርት እና የቴክኖሎጂ ልህቀት ማዕከል ሆኖ የሚያገለግል እንዲሁም የከተማችንን ዓለም አቀፍ ሚና የሚያልቅ ሲሆን ለበርካቶች የስራ ዕድል የሚፈጥር ታላቅ ፕሮጀክት ነው።
ለዚህ ስምምነት መሳካት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ላበረከቱት አስተዋፅዖ በከተማችን ነዋሪዎች ስም ላመሰግናቸው እወዳለሁ።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ