የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ፣የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ፣ባሀብቶችን እና የንግዱን ማህበረሰብ ያካተተ ልዑካን አሸባሪው የህወሓት ቡድን በከፈተው ጦርነት በአፋር ክልል ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ ለማድረግ ሰመራ ከተማ ገብቷል።
ሰመራ ሱልጣን አሊሚራህ ሀንፍሬ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ለልዑካኑ አቀባበል አድርገዋል ።