የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ፣በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የዴሞክራሲ ሰርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ አቶ መለሰ አለሙ ፣ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ ፣ከፍተኛ አመራሮች ፣ከከተማዋ የተውጣጡ ባለሀብቶች እና ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ለአማራ ክልል ድጋፍ ለማድረግ ባህርዳር ከተማ ገብቷል።
ልዑኩ ባሕር ዳር ከተማ በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል