የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተለያዩ የሃገራችን ክፍሎች በተለያዩ ጊዜያት በሚገጥሙ ሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ አደጋዎች አለኝታነቱን ሲያሳይ መቆየቱ ይታወሳል:: በዛሬው ዕለትም በሰሜን ኢትዮጵያ በጦርነቱ ለተጎዱ ወገኖች የሚሆን የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ከ650 ሚሊዮን ብር በላይ ለመስጠት ቃል ገብተዋል::
ጥሪያችንን አክብራችሁ የወገኔ ህመም የእኔም ህመም ነው በማለት የበኩላችሁን ሃገራዊ ግዴታ ለተወጣችሁ ልበ ቅን ወገኖች ሁሉ በተጎጂዎች ስም እናመሰግናለን::