የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር በሶማሌ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ሁለተኛ ዙር ድጋፍ አድርጓል::
አዲስ አበባ ከተማ የሁላችን ከተማ መሆንዋን በተለያዩ አካባቢዎች ለተከሰቱ የድርቅ አደጋዎች ድጋፍ በማድረግ አጋርነቱን ሁሌም በተግባር ያሳያል ብለዋል ከንቲባ አዳነች አቤቤ።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ዛሬ ለሁለተኛ ዙር የተደረገው 22 መኪና የመኖ እና ለሠው የሚሆን የምግብ ፍጀታ የሚውል ቁሳቁስ ለክልሉ ፕሬዝዳንት ለሙስጠፌ መሃመድ አስረክበዋል።
በመጀመሪያ ዙር የአ/አበባ ከተማ አስተዳደር ለሱማሌ ክልል 100 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን ይታወሳል ::
ከንቲባ አዳነች በሱማሌ ክልል የተከሰተው ድርቅ በሠው ህይወት ላይ ችግር እንዳይፈጥር ክልሉ ለሚያደርገው ጥረት ሁሌም ከጎናችሁ ይሆናል ብለዋል።
የሱማሌ ክልል ፕሬዚዳንት ሙስጠፌ መሃመድ ባለፉት 3 ዓመታት በክልሉ ሠላምና ልማት በርካታ ለውጥ መመዝገቡን ገልፀው ዘንድሮ የተከሰተውን ድርቅ ለመቋቋም ክልሉ የተለየ በጀት በመመደብ እየሠራ ይገኛል ብለዋል።
ባለፉት 40 ዓመታት ያልታየ ድርቅ በክልሉ ተከስቷል ያሉት ሙሰጠፌ ችግሩን ለመቋቋም ጥረት እየተደረገ መሆኑንም ገልፀዋል::
አቶ ሙስጠፌ መሃመድ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሁለተኛ ዙር ለክልሉ ያደረገው ድጋፍ በክልሉ ህዝብ ስም ምስጋና አቅርበዋል።