በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በተደረገው ጥናት ከ10ዐሺህ በላይ ዜጎች በቀን አንድ ጊዜ መመገብ የማይችሉ በመሆኑ የጎዳና ተዳዳሪዎች እና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የምገባ መርሐግብር የሙከራ ተግባር በ5 ክፍለ ከተሞች ተግባራዊ ለማድረግ ስምምነት ተፈረመ ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከተለያዪ ባለ አምስት ኮኮብ ሆቴሎች ፣አጋር ድርጅቶች እና ባለሀብቶች ጋር በመተባበር ጎዳና ተዳዳሪዎችን እና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎችን የዕለት ጉርስ የሚሆን ምግብ ለማቅረብ በሙከራ ደረጃ በአምስት ክፍለከተሞች የምገባ ማዕከል ለማደራጀት ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በተገኙበት ከባለ ኮኮብ ሆቴሎች እና አጋር ድርጅቶች ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል ።
በስምምነት መርሐግብሩ ላይ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እንደገለፁት በከተማዋ በተደረገ ጥናት ከ100ሺህ በላይ ነዋሪዎች በቀን አንድ ጊዜ መመገብ የማይችሉ ዜጎች ይገኛሉ ብለዋል ።
እነዚህን ዜጎች በቀን አንድ ጊዜ ለመመገብም በሙከራ ደረጃ በአምስት ክፍለከተሞች ተግባራዊ እንደሚደረግ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል ።