በንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በቅርቡ የስራ ዕድል የተፈጠረላት ሰሚራ መሀመድ በዛሬው ዕለት መኖሪያ ቤት ተሰጣት።
የጉዳቱ ሰለባ የሆነቸው ሰሚራ መሀመድ ቤተሰቦች፤ አመራሮችና የአስተዳደር ሰራተኞች በተገኙበት የቁልፍ ርክክብ ስነስርዓት ተከናውኗል።
የመኖሪያ ቤት ቁልፋን በስፍራው በመገኘት ያስረከቡት የንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሮ ነጻነት ዳባ አስተዳደሩ ለሰሚራ የሚያደርገውን ሁሉን አቀፍ ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
ዋና ስራ አስፈፃሚዋ አክለውም ሰሚራ ተገቢውን እንክብካቤ እና የህግ ድጋፍ እንድታገኝ ያደረጉ አካላት ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።