ክፍለ ከተማው በይፋ ስራ መጀመሩን አስመልክቶ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ለለሚ ኩራ ነዋሪዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክታቸውን አስተላልፈው፣ ክፍለ ከተማው በሙሉ አቅሙ ስራ መጀመሩን በይፋ አብስረዋል::አዲሱ ክፍለ ከተማ የለውጡ ትሩፋት ነው ያሉት ወ/ሮ አዳነች የህዝብ ጥያቄ ምላሽ ያገኝ ዘንድ የሚሰራው መንግስት የብልፅግና ጎዳናን ለማስቀጠል ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል::
የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንዲፈቱ የከተማ አስተዳደሩ ፖሊሲዎችች በመንደፍ ተግባራዊ እንደሚደረጉ እና የመሰረተ ልማት ጥያቄዎች የመመለስ ስራ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ ወ/ሮ አዳነች ተናግረዋል የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ከቦሌ እና የካ ክፍለ ከተሞች 6 ነባር ወረዳዎች እና አራት አዳዲስ ወረዳዎችን በማደራጀት የአካባቢውን ነዋሪዎች እና አርሶ አደሮች የተለያዩ አገልግሎት የሚሰጥ ይሆናል ።