ከባህር ዳር በመገንባት ላይ ወዳለው የአባይ ወንዝ ድልድይ ለመድረስ የሚያስችለውንም መንገድ ግንባታ ጎብኝተዋል። ድልድዩ 380 ሜትር ርዝማኔ እና 43 ሜትር የጎን ስፋት ያለው ሲሆን፣ መንገዱ 4.7ኪ.ሜ. ርዝማኔ አለው። ግንባታዎቹ በመጪው ዓመት የሚጠናቀቁ ሲሆን፣ የፕሮጀክቱ 62 በመቶ ተጠናቅቋል።