በብልጽግና ፓርቲ የሶማሌ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ” ድሎችን የማጽናትና ፈተናዎችን የመሻገር ወቅታዊና ታሪካዊ አመራሮች ተልዕኮ ” በሚል ርዕስ ለከፍተኛ አመራሮች የተዘጋጀ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው
በብልጽግና ፓርቲ የሶማሌ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት” ድሎችን የማጽናትና ፈተናዎችን የመሻገር ወቅታዊና ታሪካዊ አመራሮች ተልዕኮ ” በሚል ርዕስ ለከፍተኛ አመራሮች የተዘጋጀ የውይይት መድረክ በጅግጅጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
በውይይቱ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በብልጽግና ፓርቲ የሶማሌ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መሀመድ ሻሌ የሀረሪ ክልል ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ አቶ አሪፍ መሀመድን ጨምሮ የክልል፣ የዞንና የወረዳ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
ውይይት መድረኩ አመራሩ በለውጡ የተመዘገቡ ስኬቶችን በሚገባ ተገንዝቦ ለማስቀጠል ቁርጠኛ አቋም በመያዝ ፓርቲንና መንግሥትን በብቃት ለመምራት የሚያስችል የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት የሚያጎናፀፍ ነው ተብሏል።
አመራሩ እያጋጠሙን ያሉ ውስጣዊና ውጫዊ ተግዳሮቶችን በብቃት ተሻግሮ የብልጽግናን ራዕይ ከግብ በማድረስ በየደረጃ ለሚገኘው አመራር፣ አባላትና ህዝቡ በቂ ግንዛቤ በመፈጠርና ኃይል በማሰባሰብ ተጨማሪ የፓርቲና የመንግሥት ተቋማዊ አቅም እንደሚፈጠርም ታምኖበታል።