በዛሬው እለት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በቂርቆስ ክ/ በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 8 የልቤ ፋና ትምህርት ቤት ሲገነቡ የቆዩትን ዛሬ የተመረቁትን ሁለት ህንፃ ጨምሮ በአጠቃላይ አራት ህንፃዎችና 80 የጋራ መኖርያ ቤቶች የሚገነቡበትን ፕሮጀክት በቦታው ይኖሩ ለነበሩ ነዋሪዎች ደግሞ ቤቶቹን በእጣ አስተላልፈዋል፡፡
ህንፃዎቹ በተገነቡበት ቦታ ላይ ለነበሩት ነዋሪዎችም እንደ ነበራቸው መኖርያ ስፋትና መጠን በቤቶቹ በይፋ እጣ በማውጣት አስተላልፈዋል፡፡
በዚህ ስነስርዓት ላይ ንግግር ያደረጉት
ከንቲባዋ ቀበሌ ቤቶችን መልሰን በመገንባት በርካታ አቅመ ደካሞችን ህይወት እያለመለምን እንገኛለን ብለዋል፡፡ቤቶቹ ዘመናዊ በሆነ መንገድ የተሰሩ መሆናቸውን ገልፀው ፤ እንደ እቅዳችን ይሄን ቤት ለማድረስ ዛሬ አልነበረም ያቀድነው፤ ግን ልማት ላይ በተለይ ቤት ላይ የነበረው ትንቅንቅ አዘግይቶን ቢሆንም አልፈነው ነው ለዚህ የበቃው ብለዋል፡፡
ይህም እነዚህ ቤቶች ግንባታቸው ከተጀመረ በኋላ መሬቱን በሚፈልጉ በግለሰቦች ለ9 ወራት ያህል በፍርድ ቤት እግድ አስቁመው ከረታን በኋላ በአጭር ጊዜ ተገንብቶ በማጠናቀቅ ለህብረተሰቡ መተላፍ ችሏል፡፡
እንደ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች በዚህ ስራ ብቻ ሳይሆን በብዙ ስራዎቻችን ትንቅንቅ አለ ብለው ያሉ ሲሆን የሚጥለን ትንቅንቁ ሳይሆን ተስፋ መቁረጡ ነው ፤ ስለዚህም ይቻላል ብለን ከሰራን ከተባበርን ፤ ብዙ ርቀት መሄድ እንችላለን ብለዋል፡፡
ለጊዜው የሚገጥሙንን እንቅፋቶች እንደማይቻል አድርገን ሳይሆን ከእንቅፋቱ በላይ ከፍ ብለን ማሰብና መስራት ይኖርብናልም ብለዋል፡
ቤቶቹን በተመጣጣን ዋጋ ገንብቶ ያጠናቀቀው ደግሞ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን ምስጋና አቅርበዋል ፡፡
+8
Mesay Diriba, ውብ ሀገር-Ethiopia and 360 others
45 Comments
56 Shares
Like
Comment
Share