በቦሌ ክፍለ ከተማ በሚገኙ ወረዳዎች የሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች ለጀግናው የአገር መከላከያ ሠራዊት የስንቅ ዝግጅት በማድረግ ላይ ናቸው፡፡
በሁሉም የክፍለ ከተማው ወረዳዎች አሸባሪው ሕወሓት የከፈተውን ጦርነት በጀግንነት በመመከት ላይ ለሚገኘው የመከላከያ ሠራዊትና ጥምር ኃይሎች ነዋሪዎች ስንቅ በማዘጋጀት ላይ ሲሆኑ፣ ሁሉም በተሰማራበት መስክ እኩይ ሴራዎችን በማክሸፍ ለአገሩ ዘብ ሊቆም ይገባል፡፡