ከአራት መቶ ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ በጀት በልበ ቀና ባለሀብቶችና በህብረተሰብ ተሳትፎ የሚገነቡት የ90ቀናት ሰው ተኮር ስራዎች በ2016 በጀት አመት አንደኛ ሩብ አመት ለማጠናቀቅ የሚሰሩ ናቸው።
ፕሮጀክቶቹ በ3 ወራት ጊዜ ውስጥ ተጠናቅቀው በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚተላለፉ ሲሆን የወጣቶች መዝናኛ ስፍራዎች ፤ ባለ 11 እና ባለ 4 ወለል የመኖርያ ሕንጻዎች ግንባታ ፤ የአይሲቲ ፓርክ-አቃቂ ወንዝ የመንገድ አካፋይ እንዲሁም ከአምቼ ወደ ኢምፔርያል የመንገድ ዳርቻ የማስዋብ ስራን በሶስት ወራት ጊዜ ውስጥ አጠናቅቆ ለአገልግሎት ክፍት ለማድረግ በመሰራት ላይ ይገኛል።
በክፍለከተማው የዳቦ ፋብሪካ ግንባታ ፣ የተማሪዎች ምገባ ማእከላት ፣ የአረጋውያን ቤት እድሳት እንዲሁም የኑሮ ውድነቱን ለማቃለል የሚያስችሉ ሌሎች ተግባራት ላይ ትኩረት ተሰጥቶ በመሰራት ላይ ይገኛል።