በቦሌ ክ/ከተማ ለመከላከያ ሰራዊት ከ22 ሚሊየን ብር በላይ 112 በሬ እና 404 በግ እና ለምግብነት የሚውል ዱቄት፣ዘይት የተለያዮና የህክምና ቁሳቁሰ በማሰባሰብ ተሸኝቷል።
ለሰራዊቱ የተሰበሰበውን ድጋፍ ወደ ግንባር የሸኙት የቦሌ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ክብርት ወ/ሮ ዓለምፀሃይ ሺፈራው በሽኝቱ ወቅት እንደተናገሩት ክብር ለሚገባው ክብር መስጠት ኢትዮጵያዊ ባህላችን ነው።በበረሀ የሀሩሩ ፀሐይ የሌሊት ብርድ ሳይበግረው ሰራዊታችን በጦር ግንባር እያስመዘገ ያለው ድል ህዝብን በነቂስ ከጎኑ መቆሙን ያረጋግጥንበት ሲሆን የተለያየ ድጋፍ ለመከላከያ ሰራዊት ያደረጋቹ ያሰተባበራቹ ነዋሪ ህዝባችን በራሴና በአስተዳደሩ ሰም አመሰግናለሁ ብለዋል።