በቦሌ ክፍለ ከተማ በ2014 በጀት ዓመት 101 ፕሮጀክቶች ተጠናቀው በዛሬው ዕለት ለአገልግሎት ዝግጁ ሆኑ።
የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር አባይ ፕሮጀክቶቹን መርቀው በይፋ ስራ አስጀምረዋል።
19 የመማሪያ ክፍሎች እና የአስተዳደር ሕንፃዎች፣ 7 የስፖርት ማዘውተሪያ እና የወጣቶች ስብእና መገንቢያ ማዕከላት፣ አንድ ላቦራቶሪ እና የመድሃኒት አገልግሎት መስጫ ተቋም፣ የቤተ መፃሕፍት ግንባታና እድሳት፣ የ27 ሼዶች ግንባታና እድሳት ሥራዎች ከተገነቡት ውስጥ ይገኙበታል።
54 ፕሮጀክቶች የተጠናቀቁ ሲሆን፥ የ21 ኪሎ ሜትር የኮብልስቶን መንገድ ሥራ፣ የ28 ኪሎ ሜትር የፍሳሽ ማስወገጃ ቱቦዎችና ካልቨርት ሥራ እንዲሁም አምስት የማኅበረሰብ አቀፍ የፖሊስ ማዕከላት ግንባታ በህብረተሰብ ተሳትፎ መገንባታቸው ታውቋል።
በክፍለ ከተማው ሥር ያሉ ወረዳዎችን ተደራሽ በማድረግም በመንግሥት ወጪና በኅብረተሰቡ ተሳትፎ ከ101 ያላነሱ ፕሮጀክቶች በ403 ሚሊየን ብር ወጪ ተገንብተው ለአገልግሎት ክፍት መሆናቸው ተገልጿል።