የጥምቀትን በዓል ምክንያት በማድረግ ዝግጅት ከተካሄደባቸው ማዕከላት አንዱ በሆነው 6ኛው ቅርንጫፍ ላይ ወ/ሮ ሂክማ ኸይረዲን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የፐብሊክ ሰርቢስና ሰው ሀብት ልማት ቢሮ ሀላፊ በተገኙበት እንደገለፁት ” ካለን ላይ ስንካፈል የጎደለውን ፈጣሪያችን ይሞላል” ያሉ ሲሆን በዚህ በጎ አላማ ላይ የተሳተፉትን አካላት በሙሉ አመስግነዋል ።
የክ/ከተማው ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ነፃነት ዳባ በበኩላቸው በከተማችን ውስጥ እየተከናወኑ ያሉ ሰው ተኮር ተግባራት መሀከል አንዱ የሆነውና የእያንዳንዱን ቤት የሚያንኳኳው ይህ የምገባ ፕሮግራም የእርስ በእርስ ማህበራዊ ትስስራችንን የሚያጎለብት ነው ሲሉ ገልጸዋል።
በዕለቱም የማዕከሉን የምግብ ወጪ በመሸፈን ድጋፍ የሚያደርጉት አቶ ሴኩሪ ኸይረዲን የክብርት ከንቲባን ጥሪ ተቀብለው ለ1ዓመት የጀመሩትን ድጋፍ እስከ መጨረሻው ለማከናወን ቃል የገቡ ሲሆን በፕሮግራሙ ላይ የተለያዩ የስራ ሀላፊዎችና ማህበራዊ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ የዳያስፖራ ማህበረሰብ ተወካዮች ተገኝተዋል።