የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ በተያዘው በ2014 ክረምት የአረጓዴ አሻራ ልማት መርሃ ግብር ከ7.4 ሚሊዮን በላይ ችግኝ ለመትከል በ9 ችግኝ ጣቢያዎች ችግኝ የማፍላት የቅድመ ዘግጅት መደረጉን አስታውቋል፡፡
እስካሁን ከ1 ነጥብ 4 ሚሊዮን በላይ የችግኝ የጉድጓድ ቁፋሮ የቅድመ ዝግጅት ስራ ተጠናቋል ተብሏል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ም/ኃላፊ ወ/ሮ ይመኙሻል ታደሰ እንደገለጹት፡- በሚወጥለው ክረምት ከሚተከለው 7. 4 ሚሊዮ ችግኝ ውስጥ 20 በመቶ የሚሆነው የጓሮ አትክልትና ፍራፍሬ ነው ብለዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አራተኛው የአረጓዴ አሻራ ልማት ዘመቻ መርሃ ግብር ከሰኔ 18 እስከ 20 /2014 ዓ.ም ድረስ ሁሉም የህብረትሰብ ክፍሎች በተሳተፉበት እንደሚጀመርም ተገልጻል፡፡
ባለፈው ዓመት የአረጓዴ አሻራ ልማት ከተተከሉት 26 ሚሊዮን ችግኞች 80 በመቶ ችግኝ መጽደቁንም የቢሮው ም/ኃላፊ ወ/ሮ ይመኙሻል ታደሰ ተናግረዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ም/ኃላፊ ወ/ሮ ይመኙሻል ታደሰ የተተከሉ ችግኞች ከተተከሉም በኃላም ማህበረሰቡ ባለቤትነት ጥበቃና እንክብካቤ እንዲያደርግላቸው ይደረጋል ልብለዋል፡፡