ሀገራችንን እና ህዝቧን ለሚወድ እና ለሚደግፍ ሁሉ ክብር እና ምስጋናችንን እንሰጣለን። የቻይና መንግስትን በመወከል በሀገራችን እና በከተማችን የለውጡ ዋና አጋር ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት በቻይና ኤምባሲ የኢኮኖሚ እና ንግድ ቻንስለር ማዳም ሊዩ ዩ በሀገራችን የተሰጣቸውን የአገልግሎት ዘመን አጠናቀው ዛሬ ሽኝት አድርገንላቸዋል። ማዳም ሊዩ አሻራቸው አዲስ አበባ ላይ ደማቅ በመሆኑ በራሴ እና በከተማ አስተዳደሩ ስም በለውጥ ጉዞአችን የቻይና አጋርነት ተምሳሌት ሆነው ለቆዩበት ጊዜ ልባዊ ምስጋናዬን እያቀረብኩ እና በወደፊት የስራ ዘመናቸውም መልካሙን ሁሉ እየተመኝሁላቸው አዲስ አበባ ሁሌም ቤታቸው መሆኗን እንዳይረሱ ልገልፅላቸዉ እወዳለሁ።