“በነጻ መዘዋወር መብት ነው። ፍልሰት ከዚህ ዓመት በፊት ከነበረው አምስት ስድስት እጥፍ ጨምሯል። አዲስ አበባ ውስጥ ላስቲክ አንጥፈው ከሚተኙት መካከል 96% የአዲስ አበባ ነዋሪ አይደሉም። አዲስ አበባን የግጭት ማዕከል አድርጎ ለመሥራት ጥረት የሚያደርጉ ሀይሎች አሉ። እነዚህ ሀይሎች የሕዝብ በዓላት ሲኖሩ ሰኔ እና ሰኞ ገጠመ ብለው አበል ከፍለው ለመረበሽ ያሰማራሉ። የአዲስ አበባ ኗሪዎች ከጸጥታ አካላት ጋር በቁርኝት መሥራት ይኖርባቸዋል:;