በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ለመከላከያ ሰራዊት ከደጀኑ ህዝብ ከ 21 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የእንስሳትና የዓይነት ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ።
በተደረገው ርክክብ 140 በሬዎች፣ 333 በጎች 67 ፍዬሎች በይነት ደረቅ ስንቅ አልባሳት ፍራሽ ብርድ ልብስና አንሶላ ይገኝበታል።
ባለሀብቶች የሴት አደረጃጀቶች ነዋሪዎችና ተቋማት እንዲሁም ግለሰቦች በድጋፉ ላይ መሳተፋቸው ተገልጿል።
በስፍራው ተገኝተው ተቋማትንና ግለሰቦችን ያመሰገኑት የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሙሉነህ ፈይሳ እንዳሉት ለጀግናው መከላከያ ሰራዊት ያሳነውን ያልተቋረጠ ደጀንነት በሌሎች የልማትና የንቅናቄ ስራዎች መድገምና ሀገራዊ የብልጽግና ራዕያችንን ማሳካት አለብን ብለዋል።
ዋና ስራ አስፈፃሚው አክለውም በሀገራችን ላይ የተጋረጠውን አደጋ ለመመከት ህብረተሰቡ ባለሀብቶችና በየደረጃው የሚገኘው አመራር ያሳየውን ቁርጠኝነት በአጽንኦት አንስተው አመስግነዋል።