በክፍለ ከተማው ከሚገኙ አርሶ አደሮች፣ የሸማች ህብረት ስራ ማህበራት ፣ከኢንዱስትሪዎች፣ከነጋዴዎች ፣በኦሮሚያ ክልል ሰበታ ከተማ አስተዳደር ካሉ አርሶ አደሮችና ጋር በመተባበር በየሳምንቱ የእሁድ ገቢያ በጀሞ 67 ማዞሪያ፣በኦሮ ፍሬሽ፣በጎፋ ካፕ እንዲሁም በአደይ አበባ በተከታታይ ሳምንታት ሲያካሄድ መቆየቱ የሚታወቅ ሲሆን በዛሬው ዕለትም የእሁድ ገበያውን ተደራሽ ለማድረግ ተጨማሪ የእሁድ ገበያ በወረዳ-11እና 12 በመተባበር ልዩ ስፍራው ጥምቀተ ባህር አካባቢ ከላፍቶ ሀና በሚወስደው አዲሱ አስፓልት መንገድ ፀበል መግቢያ ዳርቻ ተብሎ በሚጠራው ቦታ ላይ የተለያዩ የግብርናና የኢንዱስትሪ ፣የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶችን ለማህበረሰቡ በስፋትና በተመጣጣኝ ዋጋ እየቀረበ ይገኛል፡፡
የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ንግድ ጽ/ቤት ኃላፊ ወይዘሮ እቴማ ጌታቸው እንደገለጹት የእሁድ ገበያውን ተደራሽነት በማስፋት ለህዝባችን የኑሮ ውድነት በማረጋጋት በኩል ያለው ፋይዳ እጅግ ከፍተኛ ሲሆን፤ ገበያውን ለማረጋጋት አምራቹን በቀጥታ ከተጠቃሚው ማህበረሰብ ጋር በማገናኘት በተመጣጣኝ ዋጋ የተለያዩ ምርቶችን በማቅረብ የእሁድ ገበያ ስፍራዎች ተደራሽነት የማድረጉን ስራ አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።
በቀጣይም ህብረተሰቡን የኑሮ ውድነት ለማቃለል የእሁድ ገበያን ተደራሽ የማድረግ ስራዎችን በልዩ ትኩረት እንሰራለን ሲሉ ወይዘሮ እቴማር ጌታቸው ገልፀዋል፡፡