የን/ስ/ላ/ክ/ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሙሉነህ ፈይሳ እንደገለፁት አሸባሪዉ ህዋህት ከኢትዮጵያ መንግስት የቀረበላቸዉን የሰላም ጥሪ ገሸሽ በማድረግ የናት ጡት ነካሽነቱን እንደወትሮዎ ሁሉ መቀጠሉ ይታወቃል ይህንንም ጥቃት ለመመከት የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች በመከላከል ላይ ይገኛሉ፣ለዚህም የን/ስ/ላ/ክ/ከተማ የሴት አደረጃጀቶች የስንቅ ድጋፍ ለማድርግ በዚህ በእናትነት ስሜት የተናሳቹሁበት ወኔ እሚበረታታ ነዉ በማለት ገልፀዋል።
የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ እንደተናገሩት የከተማዋ የትምህርት ተቋማት ከመማር ማስተማር ጎን ለጎን ሀገራቸውን ለመከላከል ሰራዊት ደጀን በመሆን ሀገራቸውን ከአደጋ ሊጠብቁ ይገባል ብለዋል።
ዶክተር ዘላለም አክለውም ትምህርት ቢሮው ይህን በማስተማር ኃላፊነቱን ይወጣል ብለዋል።
የን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሙስጠፈ ቱኩ እንደገለፁት የበለፅገችና ሰላሟ የተርጋገጠችን ሀገር ለመፍጥር ከጦርነት ነፃ የሆነች ሀገር መፍጠር አስፈላጊ ነዉ በማለት ገለፅዋል