በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ገብርኤል ቤተክርስቲያን አካባቢ የአሸባሪው ህወሓት ተላላኪ የሆነ ግለሰብ ራሱን ደብቆ ቄስ በመምሰል የእምነት መፅሐፍ ይዞ ሲንቀሳቀስ በፀጥታ ሃይሎች ክትትል በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡
ይህ ግለሰብ ራሱን የኦርቶዶክስ ቄስ በማስመሰል እኩይ አላማቸውን ለመፈፀም ሲንቀሳቀስ የነበረ ሲሆን በሰላም ሰራዊት አባላት ጥርጣሬ ክትትል መነሻ በፀጥታ ሃይሉ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡
በተደረገ ማጣራትም ምንም አይነት የቅስና ሙያ የሌላውና ራሱን ቀይሮ ለድብቅ አላማው ሲንቀሳቀስ የነበረ መሆኑ ታውቋል፡፡
አሁንም ህብረተሰቡ አሸባሪዎቹ የህወሓትና ሸኔ ቡድኖች የህዝባችንን ሰላም ለማወክ ምንጊዜም ያለእረፍት የሚሰሩ መሆኑን በመረዳት ከፊታችን ያሉ በዓላትም በሰላም ተጀምረው እንዲጠናቀቁ አካባቢውን በንቃት በመጠበቅ ፀጉረ ልውጦችን በትኩረት በመከታተል አካባቢውንና ከተማውን እንዲጠብቅ ጥሪችንን እናቀርባለን!!