‹‹ይህንን አመራር በሆነ ሶሻል ሚድያ ላይ በወጣ ( incident) መለካት አይቻልም፡፡ ብዙ ሃላፊነቶችን መወጣት የሚያስችል ቁመና፤ በዚያ ልክ መግባባት የቻልንባቸው መሰረታዊ ስራዎችን ለማሳካት ያደረግንበት እንደሆነ መወሰድ አለበት፡፡
በአመራራችን መሃከል በአንዳንድ አጀንዳዎች ላይ ልዩነት እንዳለ ተደርጎ ለመሳል የሚደረገው ነገር ትክክል አይደለም፡፡ እንደዚህ አይነት እምነት የለኝም እኔ፡፡
ይህንን የምልበት በተለይ ስራን ለመምራት ብቻ ሳይሆን የብልፅግናን አስተሳሰብና የብልፅግናን እሳቤዎች ለማስረፅ የሄድንበትን መንገድ ይሄ አመራር በሚገባ ሊገነዘብ ይገባል፡፡
ያ ብቻ አይደለም በብልፅግና እሳቤ ውስጥ የሚመጡ አጀንዳዎችን እንዴት መመከት እንዳለብን ጭምር የጋራ አድርገን ጋራ አመራር ነው የምንሰጠው፤ ይህንን ወ/ሮ አዳነች ልትገልፀው ትችላለች ፤መለሰ ሊገልፀው ይችላል ወይንም እኔ ልገልፀው እችላለሁ፡፡››
አቶ ጃንጥራር አባይ
የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የስራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ