የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት የመንግስት ረዳት ተጠሪና የብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ፓርቲ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ተተካ በቀለን ጨምሮ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ርክክብ ተደርጓል።
አሸባሪው ህውሃት ሁሉንም የሰላም አማራጭ ዘግቶ ኢትዮጵያን ለማፍረስ የመጣውን ጠላት የህዝብ ደጀን ይዞ እየመከተ ነው ያሉት አቶ ተተካ በቀለ ጠላትን እየደመሰሰ ለሚገኘው መከላከያ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ሐቢባ ሲራጅ አሸባሪዎቹ በበኩላቸው አሸባሪዎቹ ህውኃት እና ሸኔ ከውስጥና ከውጪ ጠላት ጋር በመተባበር ሀገር አልባ ሊያደርጉን እየሰሩ ቢሆንም በጀግኖች የቁርጥ ቀን ልጆቻችን ተጋድሎ ለትውልድ እናስተላልፋለን ብለዋል።
ሁላችንም ለሀገራችን ከመለያየት ይልቅ አብሮነትን ፣ ከመነቃቀፍ ይልቅ መከባበርን ፣ ከመገፋፋት ይልቅ መደጋገፍን ፣ ከመስረቅ ይልቅ ለፍቶ ማደርን እንዲሁም ከጠላትነት ይልቅ ወንድማማችነትን በማስቀደም በተሰማራንበት የስራ መስክ ለሀገራችን ሰላም እና ህልውና ልክ እንደ መከላከያችን ልንተጋ ይገባል ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚዋ የክፍለ ከተማው አስተዳደር ነዋሪዎች ፣ የመንግስት ሰራተኞች ፣ ባለሀብቶች እና ነጋዴዎች ከ51 ሚሊዮን ብር በላይ አሰባስበው ማስረከባቸውን ገልፀዋል።
ሰራዊቱን በመወከል ድጋፉን የተቀበሉት የመከላከያ ሰራዊት ሴቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜ/ጄኔራል ጥሩዬ አሳቼ ይህን ያልተቋረጠ ድጋፍ ሳይሰስት ለሰጠን ህዝብ ሰራዊቱም ህይወቱን ሳይሰስት በመገበርና አሸባሪዎችን በመደምሰስ የተከበረች ኢትዮጵያን ለትውልድ ለማስረከብ ከምንጊዜውም በላይ ቁርጠኛ መሆኑን አስታውቀዋል።