በአቃቂ ክፍለ ከተማ 300 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ ሰው ተኮር ኘሮጀክቶች በይፋ ተጀምረዋል።
በማስጀመሪያ ኘሮግራሙ የተገኙት የአዲስ አበባ ም/ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ የከተማዋን ነዋሪዎች የመኖሪያ ቤት እጥረት ለመፍታት በተለያዩ ኘርጀክቶች ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል።
አቶ ጃንጥራር አክለውም በክፍለ ከተማው ከፍተኛ የመልካም አስተዳደር ችግር ሆኖ የቆየው የአቃቂ የመንገድ ኘሮጀክት በፍጥነት እንዲጠናቀቅም ከተማ አስተዳደሩ ርብርብ እያደረገ ይገኛል በማለት ገልፀዋል።
የአቃቂ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር አበራ ብሩ በበኩላቸው፣ ክፍለ ከተማው የከተማዋ የንግድ መተላለፊያ ኮሪደር እንደመሆኑ የልማት ስራዎቹም በዚያው ልክ እየተሰሩ መሆናቸውን አብራርተዋል።
ከተጀመሩ ኘሮጀክቶች ውስጥም በቀን አንድ ጊዜ መመገብ ያልቻሉ ዜጎችን ለመመገብ የሚያስችሉ መመገቢያ አዳራሾች፣ ባለ 11 ወለል ወጭ ቆጣቢ የመኖሪያ ቤት ግንባታ፣ የፖሊስ ኮሚዩንቲዎች፣ የአደባባይና የመንገድ ዳር ማስዋብ ዬገኙበታል።