በአዲስ አበባ ያለ አግባብ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ፣ ሰዉ ሰራሽ የምርት አቅርቦት እጥረት በሚፈጥሩና የህዝቡን የተረጋጋ ኑሮ ለማወክ ብሎም አገር ለማፍረስ የሚደረገውን እኩይ ተግባር ለመከላከል እና እርምጃ ለመዉሰድ የተዋቀረውግብረሃይል ዛሬ ማለዳ ስራውን ገምግሟል ።
ግብረ ሃይሉ የሚመለከታቸውን አካላት በማወያየት እና እየተገባረ ባለው የቁጥጥር ስራውም የተወሰኑ ሸቀቶች ላይ የዋጋ ለውጥ መታየቱን ተረድተናል ያሉት ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በአንዳንድ አካባቢዎች የተደበቁ ምርቶችም እየተገኙ ነው ብለዋል።
በቀጣይም ቁጥጥሩ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት፣ አቅርቦትን ለመጨመር ምርት በብዛት ወደ ከተማችን መግባት እንዳለበት፣ የገበያ ቦታዎችን ማስፋት ስለሚያስፈልግ አጠናክረን እንሰራለን ብለዋል ።
ችግሩን በጋራ የመፍታት ስራ ላይ ህብረተሰቡን በተደራጀ መንገድ ማሳተፍ ያስፈልጋል በዚህም ህብረተሰቡ ጥቆማ የሚሰጥበት እና ጥቆማ ለሚሰጡ አካላት ማበረታቻ የሚሰጥበት ስርአት እንደሚዘጋጅ ምክትል ከንቲባዋ አመልክተዋል ።