በመዲናዋ የተጀመረውን የኅብረት ሥራ ማኅበራት የእሁድ ገበያ አጠናክሮ ለማስቀጠል የንቅናቄና የግብይት ትሥሥር መድረክ እየተካሄደ ነው።
በመድረኩ የኢትዮጵያ ኅብረት ስራ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አብዲ ሙህመድ ፣ ምክትል ከንቲባ አቶ ዣንጥራር አባይ እንዲሁም ሌሎች የፌደራል፣ የክልል እና የከተማ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተጀመረውን የ ”ዕሁድ ገበያ” አጠናክሮ ለማስቀጠል በርካታ ሥራዎች መሠራት እንዳለባቸዉ ተነስቷል።
የዕሁድ ገበያ በከተማዋ የሚስተዋለውን የዋጋ ንረት ለማረጋጋትና ኅብረተሠቡ በተመጣጣኝ ዋጋ ምርቶችን በቀላሉ ማግኘት እንዲችሉ አግዟል ነው የተባለው።
አቶ ዣንጥራር አባይ፥ የዕሁድ ገበያው በከተማዋ ላይ የተፈጠረዉን የዋጋ ንረት ለማርገብ አግዟል ፤ ሆኖም ግን በጉዳዩ ብዙ መሠራት አለበት ብለዋል ፤ የገበያ ትሥሥሩን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባም ነው የጠቆሙት፡፡
ገበያዉን ለማረጋጋት ከተማ አሥተዳደሩ 1 ቢሊየን ብር መበጀቱንና 500 ሚሊየኑን ለግብርና ምርቶች ማዋሉንም ነው ያመላከቱት፡፡
እስካሁን ባለዉ ግብይትም ከ “ሠንደይ ማርኬት” የ13 ሚሊየን ብር የግብይት እንቅስቃሴ እና የገንዘብ ዝውውር እንደሚከናወን ነው የተመላከተው፡፡
በከተማዋ ላይም 11 የገበያ ቦታዎች መኖራቸውንና ቁጥራቸውን ወደ 20 ለማሣደግ እየተሠራ መሆኑም ተነሰቷል።
85 የነበሩትን የኅብረት ሥራ ማኅበራት ወደ 132 ለማሣደግ እንደሚሠራም ተገልጿል።
እነዚህን ማሻሻያዎች በማከናወንም የግብይት ገቢውን ወደ 20 ሚሊየን ማሣደግ እንደሚቻልም በመድረኩ ላይ ተነስቷል።
የአቅርቦት እና ፍላጎት አለመመጣጠን ፣ የገበያ ቦታ እጥረት እና ለገበያ ምቹ ቦታ አለማግኘት በክፍተትነት የተነሱ ሲሆን ሁኔታውን ለማሻሻል እንደሚሠራም ነው የተመላከተው።
በቀጣይ በመድረኩ የግብርና ምርቶች የግዢና ሽያጭ ውል ከ100 ሺህ ኩንታል ወደ 500 ሺህ ኩንታል ለማሣደግ የመግባቢያ ሠነድ ዉል ይፈረማል ተብሎ ይጠበቃል።
በዘቢብ ተክላይ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!