ነሐሴ 12 ቀን 2014 አ.ም በእለተ ሐሙስ በአዲስ አበባ ከተማ በአንድ ጀምበር አራት ሚሊዮን ችግኞች ይተከላሉ።
ይህ ደማቅ አረንጓዴ አሻራ የማሳረፍ ታሪካዊ መርሐግብር በአዲስ አበባ ከተማ በአስራ አንዱም ክፍለከተሞች በመጪው ሐሙስ ከጠዋቱ 12 ስአት ጀምሮ ይካሄዳል።
ስለሆነም በእለቱ መላው የከተማችን ነዋሪዎች ወጣቶች፣ ሴቶች ፣ ተማሪዎች፣ የፀጥታ አካላት፣ የእምነት አባቶች፣ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች፣ ባለሃብቶች በጎ ፈቃደኞችና ሁላችሁም የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች በየክፍለከተሞቻችሁ ተገኝታችሁ ለችግኝ መትከያ በተዘጋጁ ቦታዎች ላይ ደማቅ አረንጓዴ አሻራችንን በጋራ እንድናሳርፍ በአክብሮት ተጋብዛችኋል !
ኑ አዲስ አበባን እናልብሳት!
አራት ሚሊዮን ችግኝ በአንድ ጀምበር በመትከል አረንጓዴ አሻራችን ለትውልድ የማኖር ሃላፊነታችንን እንወጣ!