ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ባስቀመጡት አቅጣጫ መሰረት የተጀመሩት የ1ወር ከ20 ቀናት ሰው ተኮር የተቀናጀ የልማት ስራዎች የሚከናወኑበት ሞዴል ክ/ከተሞችን የመፍጠር ፕሮጀክት በአምስት ክ/ከተሞች እየተከናወነ ይገኛል፡፡
በዛሬው እለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ እንዲሁም ቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው የአዲስ አበባ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ከፋተኛ አመራሮች ና የካቢኔ አባላት በተገኙበት በቂርቆስና ልደታ ክ/ከተሞች እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎችን በከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ አስጎብኝነት ተዟዙረው እየጎበኙ ይገኛሉ፡፡