በአዲስ አበባ የሃገራችንና የአፍሪካ ሃገራት መዲና ከመሆኗም በተጨማሪ የተለያዩ የኢኮኖሚና የማህበራዊ እንቅስቃሴዎች በፍጥነት እያደጉ በመሆኑ ይህን ፈጣን እድገትና ዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴ የሚመጥን ዘመናዊ የትራንስፖርት ተቋም፣ ሙሉ ለሙሉ አውቶሜትድ የሆነ የትራፊክ ፍሰት ማሳለጫና የትራፊክ ደህንነት መቆጣጠሪያ በማስፈለጉ በአሁን ሰዓት በግንባታ ላይ ይገኛሉ፡፡
ህንጻው ተገንብቶ ለአገልግሎት መብቃት ከተማዋ የትራንስፖርት ዘርፍ ተቋማት በአንድ ጣራ ስር እንዲገኙ ከማድረጉ ጋር ተያይዞ ባለጉዳዮች ሳይጉላሉ ቀልጣፋ አገልግሎት የሚያገኙበትን ሁኔታ ይፈጥራል፡፡