እስካሁን ባለው በመዲናዋ 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ችግኝ ለተከላ ዝግጁ ሆኗል።
በዘንድሮው መርሐ ግብር አገር በቀልና የፍራፍሬ ችግኞች በተለየ ትኩረት የሚተከሉ ይሆናል።
በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነ ከውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮና በስሩ ያሉ አስራ አንዱም ክ/ከተማ ተጠሪ ጽ/ቤቶች ፣ ከወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ፣ ከህብረተሰብ ተሳትፎ ጽ/ቤትና ከፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ አመራሮች ጋር በችግኝ ተከላ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችና በቢሮው በቀረበ ሪፖርት ላይ በመወያየት የቀጣይ ጊዜያት የትኩረት አቅጣጫ አሰቀምጠዋል።