የከተማ ፈጣን አዉቶቡስ ትራንስፖርት (BRT) በተለያዩ የአለማችን ክፍሎች እየተተገበረ ያለ ዘመናዊ የትራንስፖርት ሲስተም ሲሆን ራሱን የቻለ የተከለለ መንገድ፤ በቀላሉ የተሳፋሪን ፍሰት ማስተናገድ የሚያስችሉ መጠበቂያዎች፤ ከአዉቶቡስ ዉጭ የሆነ የክፍያ ስርዓት፤ለአዉቶቡስ ጥገናና ስምሪት የሚያገልግል ዴፓ ያለው፤ በመንገድ መጋጠሚያዎች ለአዉቶቡስ ቅድሚያ የሚሰጥ እና የኮሪዶር ልማትን የሚያበረታታ የብዙሃን ትራንስፖርት ዓይነት ነዉ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ የሚስተዋለውን የብዙሃን የትራንስፖርት ችግር በመፍታት ፈጣን፤ አስተማማኝ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ተደራሽ፣ወጪ ቆጣቢ እና አካባቢያዊ ተስማሚነቱ የተረጋገጠ የብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎትና ሥርዓት እንዲኖር ታስቦ 15 የBRT ኮሪደሮች ተለይተዉ በመሪ እቅዱ ላይ ተቀምጠዋል፡፡
እነዚህም፡-
1. BRT-B1፡- ከዊንጌት ተነስቶ በሆላንድ ኤምባሲ 3 ቁጥር ማዞሪያ አድርጎ አለርት አየር ጤና
2. BRT-B2፡- ከዊንጌት በመርካቶ አድርጎ ሜክሲኮ- ጎፋ ወደ ጀሞ የሚደርስ
3. BRT-B3፡- ከጉለሌ በለገሃር ጎፋ ገብርኤል አድርጎ ላፍቶ ሃና ማርያም የሚሄድ
4. BRT-B4፡- ሽሮሜዳ በአራት ኪሎ በመገናኛ አድርጎ ኮተቤ ካራሎ የሚወስድ
5. BRT-B5፡- ከመገናኛ በቦሌ ድልድይ አድርጎ ለገሃር
6. BRT-B6፡- ከጦር ኃይሎች በቄራ አድርጎ ቦሌ ድልድይ
7. BRT-B7፡- ከአየር ጤና በቶታል አድርጎ ብስራተ ገብርኤል በፑሽኪን አደባባይ ሜክሲኮ
8. BRT-B8፡- ከቦሌ በኡራኤል ካዛንቺስ በአራት ኪሎ አድርጎ ስድስት ኪሎ ፈረንሳይ የሚያደርስ
9. BRT-B9፡- ከአየር ጤና በመካኒሳ ቆጣሪ እስከ ቃሊቲ
10. BRT-B10፡- ከቃሊቲ ቦሌ
11. BRT-B11፡- ከካራሎ በሲኤምሲ ሰሚት አድርጎ በቦሌ ለሚ አይቲ ፓርክ የካ ቦሌ አራብሳ እስከ አያት
12. BRT-B12፡- ከአያት በሰሚት አድርጎ ቦሌ ወረገኑ እስከ ቂሊንጦ
13. BRT-B13፡- ከቡልቡላ በቂሊንጦ ኮዬ ፈጬ
14. BRT-B14፡- ከለቡ በአቃቂ ኮዬ ፈጬ
15. BRT-B15፡- ከኢምፔሪያል ሆቴል ጎሮ አድርጎ ቦሌ አራብሳ ናቸው፡፡