የፊታችን እሁድ በድምቀት የሚከበረውን የመስቀል ደመራ በአል አስመልክቶ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ከፍተኛ አመራሮች ከአዲስአበባ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ፤ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ የአዲስ አበባ ሀገር ስብከት ልዩ ልዩ አድባራትና ገዳማት አስተባባሪዎች ጋር ዝግጅት ስራዎች ዙሪያ ተወያይተዋል ።
የመስቀል ደመራ በዓል ሀይማኖታዊ ይዘትና ቱፊቱን በጠበቀ መልኩ እንዲከበርና ያለ ምንም የፀጥታ ችግር ምእመኑ በዓሉን እንዲያከብር የአድባራትና ገዳማት አስተባባሪዎች የበኩላቸውን ሚና እንደሚወጡ ተናግረዋል ።