የዛሬው እለት የእሁድ ገበያ ከወትሮ በተለየ መልኩ የተለያዩ የግብርናና ኢንደስትሪ ምርቶችንና ለበአል የሚያስፈልጉ አቅርቦቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ለሸማቹ ቀርበውበታል።
ከዚህ በተጨማሪ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች መጪው የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ የገበያ መረጋጋትን እና የሸማቹን ማሕበረሰብ እንግልት ለመቀነስ ያስችል ዘንድ እስከ በዓሉ ዋዜማ የሚቆይ የንግድ ባዛርም እየተዘጋጀ ይገኛል።
የከተማ አስተዳደሩም ዋጋ አለአግባብ በመጨመር የዋጋ ንረት የሚያስከትሉ ነጋዴዎችን ክትትልና ቁጥጥር እያደረገ ይገኛል።