በሁሉም ክ/ከተሞችና ወረዳዎች እየተካሄደ ባለው በዚህ ውይይት ከሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የተውጣጡ ሰፊ ቁጥር ያላቸው ነዋሪዎች በየመድረኮቹ እየተሳተፉ ሲሆን በመድረኩም የፓርቲና የመንግስት ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
በዋነኝነት የእነዚህ መድረኮች አላማ ህብረተሰቡ እንዲደመጥና ሃሳቡና አስተያየቱን በግልፅነት ለመንግስት እንዲያቀርብ በማድረግ ለቀጣይ እቅዶች እንደ ግብአት እና መነሻ አድርጎ መውሰድ ነው፡፡
ይህ መድረክ ከብልፅግና ጉባኤ መጠናቀቅ በኋላ በጉባኤው የተቀመጡ አቅጣጫዎችና ውሳኔዎችን ለህዝቡ ለማቅረብ እንዲሁም ህዝቡን ለማዳመጥ የተፈጠረ አጠቃላይ አገራዊ መድረክ ነው፡፡