መስከረም 22 በአዲስ አበባ የሚከበረውን የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል በሠላምና በተሳካ ሁኔታ ለማክበር እንዲሁም ከመላዉ ኦሮሚያ ለሚመጡ እንግዶች አቀባበል ለማድረግ የሚያስችሉ ዝግጅቶች በክፍለ ከተሞች እየተደረጉ ይገኛል፡፡
በዛሬው ዕለትም በለሚ ኩራ ፣አቃቂ ቃሊቲ ፣ንፋስ ስልክ ላፍቶ ፣በየካ እና ጉለሌ ክፍለ ከተሞች በደማቅ ስነስርዓት በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
በትላንትናው ዕለትም በአራዳ ፣በአዲስ ከተማ እና በልደታ ክፍለ ከተሞች የኦሮሞ ብሔር ተወላጆችና የተለያዩ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች በተገኙበት በድምቀት ተከብሯል፡፡