በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች የህዝብ አደረጃጀት መስርተው የአካባቢያቸውን ጸጥታ ለሚጠብቁ የህብረተሰብ ክፍሎች ስልጠና መስጠት ተጀምሯል፡፡
በዚህ መሰረት በተለያዩ ክፍለ ከተሞች እስከ ወረዳ ድረስ ተደራጅተው የአካባቢያቸውን ሰላም እና ጸጥታ ለሚጠብቁ ወጣቶች እና የህብረተሰብ ክፍሎች ስልጠና በመስጠት ላይ ነው።
ነዋሪዎች የአሸባሪውን የህውሃት ሰርጎ ገቦች ምሽትን ተገን በማድረግ የሚፈጠሩትን ወንጀሎች አስቀድሞ ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የጀመሩትን የጸጥታ ስራ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ለማስቻል ነው ተብሏል ።
ስልጠናው በማህበረሰብ ዓቀፍ በጎ ፍቃደኝነት፣ ወንጀልን መከላከልና ስነ ምግባር ላይ እንዲሁም የህዝባዊ ሃይሉ ተልዕኮ ላይ ግልጸኝነት መፍጠር ላይ ያተኩራል ።