በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ሕዝባዊ አደረጃጀቶች የተሳተፉበት በአካባቢ ሠላም እና ጸጥታ ላይ ያተኮረ ውይይት በመካሄድ ላይ ይገኛል።
የአዲስ አበባ ከተማ ሠላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ተፈራ ባለፉት ቀናት በተለያዩ ክፍለከተሞች እየተካሄዱ ባሉት የሠላም እና ጸጥታ ህዝባዊ ውይይት ላይ እንዳስታወቁት ሠላም ለማረጋገጥ የመንግስት፣ የሕዝቡና የጸጥታ አካላት ትብብር በተሻለ መጠናከሩን ተናግረዋል።
ሽብርተኞቹ ህወሓትና ሸኔ የከተማዋን ሠላምና ደህንነት ለማናጋት በተለያየ ጊዜ እኩይ ሴራዎችን ቢነድፉም ነዋሪዎች ከሌላው ጊዜ በተለየ ሁኔታ አካባቢያቸውን በመጠበቅ መክሸፋቸውን ምክትል ኃላፊዋ አስገንዝበዋል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሸነር ጌቱ አርጋው በበኩላቸው ሕብረተሰቡ በየአካባቢውን በመጠበቅ የበኩሉን አስተዋጽኦ እየተወጣ መሆኑን ገልጸው ለጸጥታ ስጋት የሆኑ አጠራጣሪ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙት ፈጥኖ ለጸጥታ አካላት ጥቆማ መስጠት የተለመደ ትብብሩን አጠናክሮ እንቀጥል አሳስበዋል።