በዛሬው ዕለትም የድል ቃልኪዳን ብስራት ቀንን በማስመልከት በመሐል ማዘጋጃ ቤት “አዲስ አበባ” ከበጎ ፍቃደኛ ወጣቶች ጋር የአዲስ አመት ዋዜማ በዓል እየተከበረ ነው።
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ በወጣቶች የእንኳን አደረሳችሁ የአዲስ አመት ስጦታ ፖስት ካርድ ተሰጥተዋል ።
አዲስ አበባ በባለፈው አመት ህብረተሰቡን በማሳተፍ በርካታ ድሎችን ማስመዝገብ መቻሉን አቶ ጃንጥራር አባይ ገልጸዋል ።
በመጪው አዲስ አመትም የከተማዋን ሁለንተናዊ እድገት ያማከሉ እና ነዋሪዎችን ተጠቃሚነት በሚያረጋግጡ ተግባራት ላይ እንደሚሰራ አቶ ጃንጥራር አመልክተዋል ።
የድል ብስራት ማብሰሪያም የቢጫ ፊኛ ወደሰማይ ለቀዋል ።