በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማችን ቀዳማይ ልጅነት እንክብካቤ ፕሮግራም ተግባራዊ የተደረገባቸው ተቋማት እየተገበኙ ነው፡፡
በጉብኝቱ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ከንቲባን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የከተማዋ የስራ ኃላፊዎች እና ፕሮግራሙን በገንዘብና በቴክኒክ ሲደግፉ የነበሩት የቢግ ዊን ፊላንትሪፒ እና ፕሮጀክቱን ለመደገፍ ፍላጎት ያላቸው የኢልማ ፊላንትሮፒ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡
ቢግ ዊን መቀመጫውን አንግሊዝ ሀገር ያደረገ ሲሆን ኢልማ ደግሞ የአሜሪካ የበጎ አድራጎት ድርጅት ነው፡፡
በጉብኝቱ በህፃናት አዕምሮ ብልፅግና ሞዴል ቅድመ 1ኛ ደረጃ የመንግስት ት/ቤቶች፣ የህጻናት እንክብካቤ ማዕከላት፣ የጤና ተቋማት እና የህፃናት የውጭ መጫዎቻዎችን እንደሚያካትት የቀዳማይ ልጅነት እንክብካቤ ፕሮግራም አስተባባሪ ዶ/ር ታቦር ገ/መድህን ገልጸዋል፡፡
አጠቃላይ ፕሮግራሙን አስመልክተው ከአዲስ አበባ ከተማ ም/ከንቲባ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ ጋር ውይይት ያደረጉ ሲሆን በአዲስ አበባ የስራ፣ ኢንተርኘራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ የተሰራውን የህፃናት ማቆያም ጎብኝተዋል፡፡