የአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ ከሀምሌ 01 እስከ ሀምሌ 30/2013 ዓ.ም በሶስቱም ደረጃ ግብር ከፋዮች ለመሰብሰብ ካቀደው 5 ቢሊዮን 390 ሚሊዮን 930 ሺህ ብር 5ቢሊዮን 820 ሚሊዮን 260ሺህ ብር ከእቅዱ 108 በመቶ መሰብሰቡን አስታወቀ ።
ከዓምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 1 ቢሊዮን 126 ሚሊዮን 950 ሺህ ብር ወይም 24 በመቶ ብልጫ እንዳለው የገቢዎች ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ ተፈራ ገልጸዋል ።
ከሀምሌ 1/2013 እስከ ጥቅምት 30/2014 ዓ.ም ድረስ ዋነኛ የግብር ማሳወቂያና መክፈል ወቅቶች ናቸው ያሉት አቶ ሙሉጌታ በተለይም ወረሃ ሐምሌ ደግሞ የደረጃ “ሀናለ ” እንደተጠበቀ ሆኖ የደረጃ “ሐ” ግብር ከፋዮች ግብሮቻቸውን የሚከፍሉበት ብቻኛ ወር ሐምሌ መሆኑም አመልክተዋል።
ባሳለፍነው 2013 በጀት ዓመት በከተማዋ 42 ቢሊዮን 606 ሚሊዮን ብር ገቢ መሰብሰብ መቻሉን የገለፁት የቢሮ ኃላፊው አፈፃፀሙም ከባለፉት 8 ዓመታት ጊዜ ከተሰበሰው ውስጥ ከፍተኛ መጠን ያለው ገቢ መሆኑን ጠቁመዋል ።