ከአራት ዓመታት ወዲህ ከ500 በላይ የሚሆኑ የእግር ኳስ፣ የቅርጫት ኳስ፣ የእጅ ኳስ ፣የመረብ ኳስ፣ የህጻናት መጫዎቻዎች እና ላይብረሪን ጨምሮ 17 አይነት አገልግሎቶችን ሊሰጡ የሚችሉ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ተሰርተው ለወጣቶች አገልግሎት መስጠት የጀመሩ ሲሆን ይህ ቁጥር በአዲስ አበባ ያሉ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን ወደ 1058 ከፍ ያደርገዋል፡፡
የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎቹ ሳምንቱን ሙሉ ለአገልግሎት ክፍት የሚሆኑ ሲሆን በአብዛኛው ነጻ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ::
በአዲስ አበባ ከሚኖሩ ህጻናትና ወጣቶች ብዛት አንጻር 1058 የመጫወቻና የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ጥቂት ሲሆኑ በሚቀጥሉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ የከተማ አስተዳደሩ የመጫወቻና የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን ቁጥር ወደ 5 ሺህ ለማድረስ ዕቅድ ይዞ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡