ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እና ከፍተኛ ሚኒስትሮች በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች በተጋለጡ ቤተሰቦች ውስጥ የሚኖሩ ሕጻናትን የእንክብካቤ አገልግሎት የሚሰጥ ቀዳማይ የልጅነት ዕድገት ፕሮግራም በዛሬው እለት በይፋ ተጀምሯል ።
የከተማ አስተዳደሩ ለህጻናት ትኩረት የሚሰጥ እና ከተማዋ ለህጻናት አመች እንድትሆን በልዩ ሁኔታ የሚታቀፉ ከ 330 ሺህ በላይ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ውስጥ የሚገኙ ቤተሰቦችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ፕሮግራም መሆኑን ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል ።ፕሮግራሙ ህጻናት ተወልደው እድሜያቸው ስድስት አመት እስከሚደርስ ፍቅር ፣ የተመጣጠነ ምግብ ፣ አእምሮአቸው እንዲነቃቃ እና እንዲበለጽግ ተገቢውን እንክብካቤ መስጠት ያስችላል ብለዋል።