የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተናን ለማስፈጸም በከተማ አስተዳደሩ ከተዋቀረው የኮማንድ ፖስት አባላት ጋር ውይይት ተካሂዷል፡፡
ከጥቅምት 29 – ህዳር 2 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጠዉ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ስኬታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በመሰራት ላይ መሆናቸዉን የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡
የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና በከተማ ደረጃ በስኬት እንዲጠናቀቅ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተከናውነዋል ያሉት የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ አንዳንድ የግል ትምርት ቤቶች ግን እስከ አሁን አድሚሽን ካርድ ለተማሪዎች አለማድረሳቸውን ጠቁመዋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ በ62 የፈተና ጣቢያዎች 36,415 ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ፈተና እንደሚወስዱ እና ይህንንም የሚመሩና የሚያስተባብሩ 2ሺ 600 የፈተና አስፈጻሚዎች ምልመላ መካሄዱን ቢሮው ገልፆል፡፡