በሁሉም ክፍለ-ከተሞች ማሕበረሰቡን በማሳተፍ የኢሬቻ በዓል ተሳታፊዎችን ሞቅ ደመቅ ባለ ሁኔታ አቀባበል የተደረጉላቸው እና በዓሉ ተከብሮ እስኪጠናቀቅ የአካባቢያቸውን ሰላም በመጠበቅ፤በፍፁም ኢትዮጵያዊ ጨዋነት እና እንግዳ ተቀባይነት አንግዶችን ተቀብለው ሲያስተናግዱ የሰነበቱ እንደነበር ይታወሳል።
ከበዓሉ በሰላም መጠናቀቅ በኋላም የኢሬፈናውን ስፍራ ጨምሮ በሁሉም ክፍለ-ከተሞች የፅዳት መረሀግብር ተከናውኗል።
የፅዳት መርሃ-ግብሩም በክፍለከተሞች አስተባባሪነት የተለያዩ የመንግስት የስራ ሐላፊዎች የእምነት ተቋማት ተወካዮች፣መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት እና በማሕበረሰቡ ተሳትፎ የተከናወነ ነው።