በአዲስ አበባ ከተማ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰና የንብረትና ሕይወት ስጋት እየሆነ የመጣውን የክረምት ጎርፍ አደጋ ለመቅረፍ አስተዳደሩ በዚህ ወቅት ቅድሚያ በመስጠት የበለጠ አደጋ ሊያስከትሉ ይችላሉ ያላቸውን ቦታዎች በመለየት የጎርፍ አደጋ መከላከል ግብረ ሃይል ተቋቁሞ ወደ ተግባር ገብቶ በርካታ ስራዎችን እያከናወን ነው።
በዚህም መሰረት በከተማው ለጎርፍ ተጋላጭ ሊሆኑ የሚችሉ ቦታዎችን በዝርዝር በመለየት የተለያዩ የቅድመ መከላከል እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ሲሆን ፡ በከተማው ለጎርፍ ተጋላጭ በሚል በለያቸው ቦታዎቸ እንደ የሁኔታው የአጭር ጊዜና የረጅም ጊዜ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ወደ ተግባር በመግባት ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡
ስለሆነም ህብረተሰቡ ከወዲሁ በክረምቱ ለጎርፍ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች የተለየ ጥንቃቄዎችን እንዲያደርግ እያሳሰብን መንግስት እንደየአካባቢዎቹ ተጨባጭ ሁኔታ አስፈላጊ ነው ብሎ የሚያምንባቸውን የመፍትሄ አቅጣጫዎች ለመተግበር ተባባሪ በመሆን ሊያጋጥሙ የሚችሉ አደጋዎችን በጋራ እንድንከላከል የከተማ አስተዳደሩ ያስታውቃል፡፡
የክረምት የጎርፍ አደጋዎችን በጋራ እንከላከል!!