ክፍለ ከተማው ለመከላከያ ሰራዊት ከነዋሪዎች ያሰባሰበውን ከ70ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት አስረክቧል ።
በመረሐግብሩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባና የስራ እድል ፈጠራ ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ አሸባሪው ትህነግን በመጠቀም ኢትዮጵያን እንደዳቦ ቆርሰው ሊውጧት የሚቋምጡ የውጪ ሃይሎችን አሳፍረን ለመመለስ ሁላችንም በአንድነት ተነስተን ለሀገራችን ህልውና መፋለም አለብን ብለዋል፡፡
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ሽታዬ መሃመድ በበኩላቸው ነዋሪዎች ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ከማድረግ ባለፈ በግንባር በመዝመት እና የአካባቢያቸውን ሰላም እና ጸጥታ በመጠበቅ በሰርጎ ገቦች የተደገሰውን በርካታ ሴራዎች ማክሸፋቸውን ገልጸዋል ።
አካባቢዎን ይጠብቁ
ወደ ግንባር ይዝመቱ
መከላከያን ይደግፉ