የትግራይ ህዝብ በአሸባሪው ህወሃት ቀንበር ስር እየተሰቃየ በመሆኑ የፌደራል መንግስት ሊደርስለት ይገባል ሲሉ ተወያዮቹ ጠይቀዋል፡፡
*******************************
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ስንታየሁ ደስታ በበኩላቸው በጦርነት ተወልዶ በጦርነት ያረጀው አሸባሪ ህወሃት በትግራይ ህዝብ ስም እየነገደ ህዝቡን ለዘርፈ ብዙ መከራ እየዳረገው በመሆኑ ከፌደራል መንግስት ጎን ተሰልፈን ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከትግራይ ህዝብ ጫንቃ ልናነሳው ይገባል ሲሉ ገልፀዋል፡፡
በውይይቱ የተሳተፉ የትግራይ ተወላጆች በበኩላቸው ህወሃት የትግራይን ህዝብ ከወንድም ህዝቦች ጋር ደም ማቃባቱ ሳያንሰው ለግል የስልጣን ፍላጎቱ ሲል ህዝቡን በግዳጅ ለጦርነት እየማገደ እያሰቃየው በመሆኑ የፌደራል መንግስት ሊደርስለት ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ተወያዮቹ አክለውም ከመንግስት ጎን በመሰለፍ የአካባቢያቸውንና የሃገራቸውን ሰላም እንደሚያስከብሩ ተናግረዋል፡፡
ውይይቱን የመሩት የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ አቶ አብዱልሰመድ ሻሚል መንግስታችን ከምንም ነገር በፊት ለሰላም ቅድሚያ ሰጥቶ የሚሰራ ቢሆንም የመንግስትን የሰላም ጥሪ እንደፍርሃት የቆጠረው አሸባሪ ሃይል ተደጋጋሚ ትንኮሳ እየፈፀመ በመሆኑ በኢትዮጵያዊነቱ የማይደራደረው የትግራይ ህዝብ ይህንን ሽፍታ ቡድን በቃህ ሊለው ይገባል ብለዋል፡፡